አደግን ተመነደግን (Satire)

Standard
እውቀት የዘለቀው መሪ ስለሰጠን
በጣም ይገባናል ፈጣሪን ማመስገን
አይገኝም ከቶ እንደ ኣያ መለስ
እንኩዋንስ በአፍሪቃ - አለም ቢታሰስ ...
	ደግሞም ከእውቀት በላይ ወሬ ሲያውቁበት
	ተናግረው አይጠግቡም ፣ ስለ ህገር እድገት
		“አደግን ተመነደግን ለሰማይ ቀርበናል
		'ኢሊትም' ተብለናል ፣ አለም ቀንቶብናል!
		አምልጠንም ወጥተን ከተረጂነት
		ባህላችን ነውና ሲራቡ ማብላት
		እንደ ሳኡዲ ላሉ ለተቸገሩት
		ለመስጠት ደርሰናል ማደሪያ መሬት፡፡
		ደስ ይበልህ ህዝቤ!!!
		በተቀረው መሬት …
		ለደስታ መግለጫ አበባ ዘርተናል
		በዚህ ጥጋብ ዘመን እህል ምን ያደርጋል?”
ሃብቱ እንደበዛለት ጎተራው እንደሞላ
ባሳሰቡት ቁጥር ያለበትን ተድላ
እያብሰለሰለ የጥጋቡን ኑሮ
ወገን ተሰቃይቶአል ቁንጣን ተወጥሮ፡፡
	በልቻለሁ ካሉት ሆድ ባይርበውማ
	ሃገር አድግዋል ሲሉ ቢበለፅግማ
	ልቦለድ እንደ እህል ደግፎ ቢያኖር
	ይሄ ተረት ተረት ባልከፋ ነበር፡፡

ልሳን (2002 እ.ኢ.አ)

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s